ሊሴ ፓሴ ለማመልከት


* የአገልግሎት ጊዜውን ያበቃ ፓስፖርትዎ ለማሳደስ በቂ ጊዜ ከሌለዎትና በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገርቤት ለመጓዝ ከፈለጉ ሌሴ ፓሴ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

* ሊሴ ፓሴው ለአንድ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡
*
የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ የጉዞዎ ቀን ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ የከፈሉበትን ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን መረከብ ይችላሉ።
*
ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1)
ሁለት (2) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ 6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2)
አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ 
3)
በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የግሪን ካርድ ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት I-94 ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ
4)
የአገልግሎት ክፍያ 50 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ 
5)
መጠየቂያ ቅጽ መሙላት 

6) አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ


~Download Pdf pr.jpg
~Download Pdf pr1.jpg
Back to Home

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   102
THIS WEEK:   525
THIS MONTH:   2081
THIS YEAR:   2081
TOTAL:    68071
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts